Sunday, December 9, 2012

የሰሞኑ ጋዜጦችና መጽሔቶች




ላይፍ መጽሔት
·         የ‹‹ሰው ለሰው›› ድራማ ቀጣይ ድራማዎች
‹‹ሰዎቹ መካሪ የላቸውም እንዴ›› አስተያየት ሰጭዎች፤
መስፍን ጌታቸው የፍቅር ጥያቄ አቅርቦልኝ  አልተቀበልኩትም›› ተዋናይት ብስራት ገመቹ፤ ‹‹ሚዛናዊ የሆነ ዘገባ ብትሰሩ ትሩ ይመስለኛል››  ደራሲ መስፍን ጌታቸው፤
·         የአባ ጳውሎስ ተተኪ የመምረጥና የእርቅ ፈተና፤ ማን መንበሩን ሊያገኝ ይችላል?
‹‹ጉባዔ ካህናት ወመምዕናን ለቤተክርስቲን ሠላም›› ትውልድ የሚወርሰው እርቀ ሰላም በሁለቱ ሲኖዶሶች እንዲወርድ ጠየቀ፤
·         ‹‹የስኬትን መንገድ ጀመርኩት እንጂ አልደረስኩበትም›› ተዋናይ ሄኖክ ብርሃኑ
·         የኢትዮጵያ ዘመናዊ የህጻናት የውጭ ንግድ፤ መንግስት ችላ ያለው የሞት መንገድ፣
·         በሕግ የበላይነት እየተሳለቁ እስከመቼ?
o    በድብደባ የስድስት ወር ጽንስ አስወጥቶኛል፣
o    የባለቤቴንና የልጄን ብልት በአጎበር ገመድ ጎትቶታል ተባባሪዎቹ አልተያዙም፣
o    የሰሻለ ህክምና እንዳገኝ ሕዝብ ይተባበረኝ›› ወ/ሮ ወርቅነሽ አድማሱ፣
·         የትራንስፖርት ትርምስ እስከመቼ?
·         ‹‹መድረክ ከኢህአዴግ ጋር ሊያላትመን ይፈልጋል›› በ1997 ኢህአዴግን በመወከል በደብረብርሃን ላይ ተወዳድረው የነበሩት ወ/ሮ የሺ ፈቃደ የኢትዮጵያ ምርቻ ቦርድ የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪ
·         ሌላም፣ ሌላም…


ቃልኪዳን መጽሔት

·         የወር ፈቃድ የተከለከለችው የቤት ሠራተኛ በአሰቃቂ ሁኔታ የአራት ሰው ሕይወት አጠፋች፤ ሰይጣን እርሷን አሳስቷት! ወይስ እርሷ ሰይጣንን አሳስታው!?
‹‹በቤቴ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው፤ አሁን ከምንም በላይ የምጠብቀው የእግዚአብሔርን ፍርድ ነው›› በአንድ ሌሊት ሙሉ ቤተሰቡን ያጣው አቶ መላኩ አማረ
·         ‹‹ኩኩ ሰብስቤ ሙሉቀን መለሰን ታደንቀው ነበር ወይስ ታፈቅረው››፤ ሙሉቀንስ የሚያፈቅራትን ሴት እንዴት አጣት - በተመስገን ባዲሶ
·         ቴዲ-አፍሮና …ቴዲ ታደሰ በአትላንታ ተፋለሙ - በተመስገን ባዲሶ
·         ‹‹የሰው ለሰው›› ድራማ አርቲስት የወሲብ ትንኮሳ
·         ‹‹የሀገሬን ሙዚቃ አስተዋውቃለሁ›› ድምጻዊት የኔነሽ መላኩ(ከናይሮቢ) ቃለመጠይቅ
·         ‹‹የጊዮርጊሱ አቼኖ እና የቡናው አዳነ ወደ አዲስ ሥራ›› በተመስገን ባዲሶ
·         ‹‹ሰባት ሺ ብር ይዞ በጠኔ ሞተ!!›› በተመስገን ባዲሶ
·         ‹‹ራሱን ለመድገም የተዘጋጀው የግብጽ አብዮት›› በሰለሞን ግርማ
·         ሌላም፣ ሌላም…

ቆንጆ መጽሔት

·         ርዕሰ አንቀጽ ‹‹ለውለታቸው ዋጋ ያጡት እቴጌ››
·         ‹‹አልጄዚራ አባይ ላይ ምን ሸተተው?›› ፍኖት አያሌው
·         ለዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ስልጣን ይገባል?
·         ‹‹ኧረ ለምን ይቅር ይኑር እንጂ ምርጫ
ገጽታ መገንቢያ ብድር ማሳላጫ!!›› እንድርያስ ተረፈ
·         ‹‹ግብጽ እያሰላሰለች ወይስ እያዘናጋች›› የኔነህ ታደሰ
·         ኃ/ማርያም ደሳለኝ ስለምን የውዝግብ ኢንኩቤተር ይሆናሉ
·         ‹‹የሠራዊት ሥርወ -መንግስት›› ዓይናለም (ከሰበታ)
·         ‹‹ተፈራ ዋልዋ የት ገቡ ከየትስ ተከሰቱ›› በቃልኪዳን አማረ የሚናፈቅ ጠፋን ማለት ነው
·         በአደባባይ የተገደለችው ሴት ጉዳይ
·         ‹‹የሁለት ሀውልቶች ስጋታዊ ወግ›› ዳግማዊ ቴዎድሮስ
·         ‹‹የጸደይ ዲያሪ›› ከቤዛ ተከታታ መጣጥፍ
·         ‹‹ኢቴቪ የኢህአዴግ ባለስልጣናትን ጃም ሲያደርግ ‹‹ከኢህአዴግ በላይ ኢህአዴግ ለመሆን የሚታትረው ኢቴቪ›› በአክሊሉ ሙሉነህ
·         ‹‹ሽንትና ጦርነት ጊዜ አይሰጥም›› በአስፋው ስለሺ
·         ጅዳ ተርሚናል የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ታሳሪዎች (ድምጹን የጻፍኩት ቃል በቃል ነው)
·         ሌላም፣ ሌላም…

ዕንቁ መጽሔት

·         ርዕሰ አንቀጽ፤ ‹‹የፑሽኪንን ሐውልት ከተነሳበት ሳይመለስ ሌሎች ሐውልቶች መነቀል የለባቸውም!››
‹‹ከሁለቱ ሐውልቶች ጀርባ›› አቡነ ቄርሎስ ግብጻዊ ናቸው ለኢትዮጵያ የሚገዳቸው ነገር የለም›› ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ
·         ቴዲ በአሜሪካ ሰርፕራይዝ የሠርግ ግብዣ ተደረገለት
·         ‹‹ከእርቀሰላምና ከፓትርርክ ምርጫ ማን ቢቀድም ይሻላል›› በአባነህ ካሴ
·         ‹‹መቃብር ያልገደበው የመለስ አገዛዝ፤ ግን እስከመቼ›› ሬኔ ሌፎርት ትርጉም በፍጹም ብርሃን
·         ‹‹የሰሞኑ ሹመት ሕገ መንግስቱን በግልጽ የሚጻረር ነው›› ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
·         ‹‹ሹመቱ የፖለቲካ ትኩሳቱን ለማብረድ ተፈልጎ የተደረገ ይመስለኛል›› ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም
·         ‹‹የኦል አፍሪካን አርት  ፌስቲቫል አርቲስቲክ ዳይሬክተሩ እኔ ነኝ›› መራሄ ተውኔት አባተ መኩሪያ
·         ‹‹የወንደላጤው ማስታወሻ›› አሸብር በቀለ ካለፈው የቀጠለ መጣጥፍ
·         ‹‹ወርቅ የማይገዛው አገልግሎት›› በዳንኤል ክብረት
·         1950-2005 ዶር መሰረት ቸኮል፡- ጋዜጠኛ ፣መምህር፣ የማሕበረሰብ አገልጋይ (ዳሰሳ)
·         ‹‹የእርቀ ሰላሙ አንቅፋት ማነው››  መንግስት፣ አቡነ መርቆሬዎስ፣ የኢትዮጵያ ሲኖዶስ፣ ስደተኛው ሲኖዶስ፣ ሕዝቡ፣ ካህናቱ በታዴዮስ ግርማ
·         ሌሎችም

አዲስጉዳይ መጽሔት

·         ርዕሰ አንቀጽ፤ ‹‹ከመጋረጃው ጀርባና ከፓርላማው ፊት›› በሚል ርዕስ የሰሞኑን የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት ይተቻል ‹‹በቅርቡ የተካሄደው የመሪዎች ሹመት ይፋ የሆነ ከመሆኑም በላይ አከራካሪነቱም ግልጽ ነው፡፡ በመሰረቱ በሰለጠነው ዓለም የሚደረገው አንድ ሰው ከፍተኛ የመንግስት ስልጣን የሚይዘው በችሎታው መሆን ሲገባ  አሁን እያስተዋልን ያለነው ግን የተለመደውን የኢህአዴግ የብሔር ሚዛን ማስጠበቅንና የቆዩ ባለስልጣናትን በወጣቶች መተካት ብቻ ታሳቢ ያደረገ ይመስላል፡፡ በተረፈ ተገቢውን ሰው በተገቢው ቦታ ከማስቀመጥ ይልቅ በአሁኑ ሹመት እንደታየው ባልተጠበቀ ሁኔታ አንዳንዶቹ ባለስልጣናት ከትምህርታቸውና ከዝግታቸው ጋር በማይጣጣም ቦታ ላይ ተቀምጠዋል፡፡››
‹‹ከሹመቱ በስተጀርባ›› የስልጣን ክፍፍል፣ የብሔር ተዋጽዖ- የቡድን አመራር ሽኩቻ
·         የታፈኑ እውነቶች በሚለው ዓምዱ ሥር ‹‹ሥራ አልባ መሥሪያ ቤቶች›› በሚል በመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ያለውን የስራ ተነሳሽነት ማጣትና የሚመጥናቸውን ሥራ ማከናወን አለመቻላቸውን ይዳስሳል፡፡
·         ጤናማ ውበት በሚለው የዶ/ር ብርሃኔ ረዳኢ ዓምድ ‹‹የዕንቁላል ቀጠሮ›› በሚል ስም ሰፍሯል ባስጡም አንድ ወዳጁ ስለሴቶች ማርፈድ የሰጠው ትንታኔ፡- ‹‹ለምን እንደሚያረፍዱ ታውቃለህ…ይኸውልህ ተፈጥሮአዊ በቀል ነው…በአዳምና ሄዋን በዘር መካከል መቀጣጠር ከጀመሩ የትየሌለ ዘመን ሆኗቸዋል፤ ግን ምን ያደርጋል የእነሱ የዘር ፍሬ (ዕንቁላል) አብዛኛውን ጊዜ ቀንና ሰዓቷን አክብራ በተቀጣጠሩበት ሰዓት ትጠብቃለች ፤ አጅሬ የወንድ ዘር ሲለው ተንቀራፎ፣ አርፍዶና ደካክሞ ይመጣል፡፡ ሲለው ከነአካቴውም ብቅ አይልም፤ በዚህም የተነሳ በሰውነት ደረጃ እኛም በተራችን ሁሌም እንጠብቃለን፡፡ መጠበቅም አለብን››
·         ‹‹መድኃኒቱን መስጠት ካልቻልን አለመመርመሩ ይሻለናል›› ዶ/ር አባተ ባኔ የጉበት በሽታን በተመለከተ በሰጡት ቃለመጠይቅ
·         በሃይማኖት ካባ ስር ጸያፍ ፖለቲካ ከሰለሞን ተሰማ ጂ
·         ‹‹ከጣራ እስከ ጉዛራ-2›› በዳንኤል ክብረት
·         ‹‹ፍቅርና ወንጀል›› በመስፍን ሃብተማርያም
·         ‹‹ልቀቁን እንጂ  አትልቀቁብን-ዶሃ›› በጌታቸው አሰፋ ዶ/ር
·         ‹‹ሦስቱ ባዶ ወንበሮች›› በኤፍሬም እሸቴ
·         ‹‹ተዝቆ ከማያልቀው ሶፍትዌር ገበያ አፍሪካ ምን አገኘች ኢትዮጵያስ የት ናት››
·         ‹‹የተከበሩት›› እና ቡጡ አንድም ሁለትም በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር
·         ‹‹ቃልና የቋንቋ ቅንቅኖች›› በበቀለ መኮንን
·         ሌሎችም…

ሪፖርተር ጋዜጣ (ረቡዕ ህዳር 26 ቀን 2005 ዓ.ም)
·         ርዕሰ አንቀጽ ጠንካራ አፍሪካዊ ሚና የሚያጫውተን ጠንካራ ኢትዮጵያዊነት እንፍጠር!
·         ንግድ ባንክ 40/60 ቤቶች ፕሮጀክት 1.12 ቢሊዮን ብር ብድር ፈቀደ
·         ባንኩ ምን ያህል ገንዘብ ለሚቆጥቡ ቅድሚያ እንደሚሰጥ አልወሰነም
·         የአዲስ አበባ አስተዳደር የሚድሮክ እህት ኩባንያን አስጠነቀቀ
·         የዲቪ ሎተሪ እንዲቆም ተጠየቀ
·         25 አውቶብሶች በአምስት መስመሮች ሥራ ይጀምራል
·         የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ የኢንቨስትመንት ደንብ ሊያወጣ ነው
·         በጥቅምት ለብሔራዊ ባንክ መቅረብ የነበረበትን ያህል ወርቅ ሳይቀርብ ቀረ
·         [ለአገሪቷ ወፎች ቁጥር መመናመን ቻይናዎች በምክንያትነት ይጠቀሳሉ]
·         አቶ መንግሥቱ ወንዳፍራሽ፣ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማኅበር ዋና ዳይሬክተር
·         ‹‹ሰዎች ከሚፈጥሯቸው ችግሮች አንዱ ደግሞ አገሪቷ ውስጥ የሚኖሩት ቻይናዎች ናቸው:: እነዚህ ዜጎች ትልቅ ቦርድ ላይ ሙጫ ነገር ለቅልቀው እህል ይበትኑበታል:: ወፎቹም እህሉን አይተው ለመብላት ቦርዱ ላይ ሲያርፉ እግራቸው ስለሚጣበቅ
·         ቻይናዎቹ ወፎቹን ለቅመው ይበሏቸዋል::>>
·         ‹‹ጂቡቲ ወደብ የሚመላለሱ ተሽከርካሪዎች የኤሌክትሮኒክስ መቆጣጠሪያ እንዲገጥሙ ሊገደዱ ነው፡፡››
·         ‹‹የኃይለ ማርያም ካቢኔ አወቃቀር›› በሰለሞን ጎሹ
·         ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኃይል መቆራረጥን ለማስቀረት መንግሥት ትኩረት ይሰጣል አሉ፡፡››
·         ኢትዮጵያ ከነፋስ ኃይል 1.3 ሚሊዮን ሜጋ ማመንጨት እንደምትችል ተጠቆመ
·         ለአዳማ ሁለት ፕሮጀክት ብድር ተገኘ - ከአቶ ኃይለ ማርያም ንግግር አስገራሚ የነበረው ይለናል ሪፖርተር
·         ‹‹ኢትዮጵያ ከንፋስ ኃይል 1.3 ሚሊዮን ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደምትችል መናገራቸው ነው:: የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ኃላፊዎች ሲናገሩ የቆዩት፣ አገሪቷ ከንፋስ ኃይል 10,000 ሜጋ ዋት ብቻ ማመንጨት እንደምትችል ነበር:: በመሆኑም አቶ ኃይለ ማርያም የጠቀሱት አኀዝ አነጋጋሪ ሆኖአል:: ይሁን እንጂ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ምሕረት ደበበ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የተናገሩት ትክክል እንደሆነ አረጋግጠውልናል:: “የኤሌክትሪክ ኢንዱስትሪ በጣም ተለዋዋጭ ነው፤ያሉት አቶ ምሕረት 
·         ሌላም፣ ሌላም…

‹‹ውሸትን ብቻ ነው የምንፈራው›› የሚል መፈክር ያላቸው ኢትዮ ቻናሎች ‹‹ፈቃዳቸውን አድሰው ይሆናል›› ተመልሰዋል፤
·         ርዕሰ አንቀጽ፤ ‹‹የግሉን ፕሬስ ማነቆዎች ዝም ብለን የምንመለከተው አይሆንም!››
·         ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ‹‹አስመራ ሄጄ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ለመወያየት ዝግጁ ነኝ›› አሉ ቃለ ምልልሳቸው ዛሬ በአልጀዚራ ቴሌቪዥን ይሰራጫል ፤ ተሰራጭቷል
·         ‹‹የ‹‹ሰው ለሰው›› ድራማ ፕሮዲውሰሮችን ማስጠንቀቂያ አልቀበለውም›› አርቲስት ብስራት ገመቹ
ሕዳር 24፣2005 በተጻፈ ደብዳቤ ስማቸሁን እንዳጠፋሁ በመግለጽ  በኤፍኤም 96.3 እና 102.1 ላይ በተከታታይ ለ4 ጊዜያት ያህል በይፋ ይቅርታ እንድጠይቅ ይህንን የማላደርግ ከሆነ በወንጀልና በፍትሃብሔር እንደሚከሱኝ የሚስጠነቅቅ ነው
·         በፍጹም የስም ማጥፋት አልፈጸምኩምም የምትለዋ አርቲስት መስፍን ጌታቸው ከሰራቸው ጥፋቶች አንጻር ለሚዲያ አይቀርቡም ብዬ የተውኳቸው አሉ ለፍርድ ቤት ግን ክሴ ላይ አቅርቤያለሁ ብላለች
·         አወዛጋቢው የፕሬዚደንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ደብዳቤ ‹‹ደብዳቤውን የጻፍኩት በስሜታዊነት ነው›› ያንግ ባይ ኸርት
·         የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን አባቶች የእርቀ ሰላም ውይይት በዳላስ እተከናወነ ነው   
·         ኢትዮጵያ ከቀንደኞቹ ሙሰኛ አገሮች ተርታ ተሰለፈች
·         ‹‹በሙስና ከ176 አገራት 113ኛ ደረጃን ይዛለች›› ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል
·         ‹‹ውጤቱን ለመቀበል ይቸግረኛል…›› የፌዴራል ስነ ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን
·         የ40/60 የቁጠባ ቤቶች ምዝገባ የት ነው?
‹‹ኃላፊነታችን ግንባታውን መከታተል እና ሲጠናቀቅ ለንግድ ባንክ ማስረከብ ነው›› የአዲስ አበባ የቤቶች ቁጠባ ኢንተርፕራይዝ
‹‹ምዝገባ ለማካሄድ ከኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ትዕዛዝ እየጠበቅን ነው›› የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
‹‹ምዝገባ መጀመር እኛን አይመለከትም›› የኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ሚኒስቴር
·         ሌላም ሌላም

ኢትዮ-ምኅዳር ጋዜጣ (ማክሰኞ ኅዳር 25 ቀን 2005 ዓ.ም)

ጀማሪ የማይመስለው ኢትዮ ምኅዳር ጋዜጣ በማክሰኞው እትሙ፣
·         ርዕሰ አንቀጽ፤ ‹‹መንግስት ሕገ-መንግስቱን የማክበርና የማስከበር ግዴታውን ይወጣ››
·         ‹‹በኢትዮጵያ የብሔርና የዘር ክፍፍልና የዘር ጥላቻ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል›› ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም
·         ሹመቱ ሕገ-መንግስቱን የጣሰ ነው
·         ጠ/ሚ ኃይለማርያም የአሰብን ጥያቄ የሚያነሱበት ጊዜ አሁን ነው፡፡
·         ግብጽ ኢትዮጵያን በጦር ትወራለች ማለት ያጠራጥራል፤
·         ኢህአዴግ በፍትሕ ላይ ቀልዷል
·         ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በድጋሚ ተከሰሰ
‹‹ከወህኒ ቤት የተለቀቅኩት መንግሥት ስህተቱን ስላመነ ነው››
‹‹ይሄ ክስ ሆን ተብሎ አዲስ ታይምስን ልክ እንደ ፍትህ ጋዜጣ ለማፈን የተደረገ ሙከራ ነው››
·         ቀሲሱ በሚያገለግሉበት ቤተክርስቲያን ተደብድበው ተገደሉ
·         ‹‹ግልጽ የሆነ ሕገ-መንግስታዊ ጥሰት ያሳየ የስልጣን ክፍፍል›› አስራት አብርሃም ሲብራራም ኢህአዴግ ሕገ-መንግስቱን የሚጥሰው ለምንድነው ብለን ብንጠይቅ የመጀመሪያውና ዋናው ምክንያት ሕገ-መንግስቱን ከራሱ ሕልውና በላይ ስለማያየው ነው፡፡ ሕልውናው ላይ ፈታኝ የሆነ አደጋ ሲከሰትና በሕገ-መንግስቱ መቀፍ ውስጥ ሆኖ ያ ፈታኝ አደጋ ሊፈታተነው የማይችል ሆኖ ከተሰማው በቀጥታ ሕገ-መንግስቱን ወደ መጣሱ ይገባል፡፡ ለዚህ በጣም ጥሩ ማሳያ የሚሆነው በ1993 ዓ.ም የህወሓት የክፍፍል ወቅት ነው ክፍሉ ጡዘት ሰማይ በነካበት ልዩነቱን ማስታረቅ በማይቻልበት ደረጃ ላይ በደረሰበት ወቅት …አንዱ ሌላውን ለማስወገድ ጥረት በሚደርግበት ወቅት ነበር ለዚህም ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ውስጥ ሁለት ሶስተኛውን የድጋፍ ድምጽ ማግኘት ያስፈልግ ነበር፡፡ በወቅቱ ነበሩት የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሰላሳ ሲሆኑ ሁለቱ ቀደም ብሎ ከማዕከላዊው ኮሚቴ ታግደው ነበር፤ ቀሪዎቹ ደግሞ አስራ አምስት ለአስራ ሁለት ሆነው ነው የተከፈሉት፡፡ አንዱ ሌላውን ለማገድ ቢያንስ የሃያ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ድጋፍ ማግኘት ግድ የሚል ነበር፤ ይህ ቁጥር ደግሞ አንዳቸውም አልነበራቸውም፡፡

ይህ በሚሆንበት ጊዜ የሚኖረው ብቸናው አማራጭ የድርጅቱን ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ ጉዳዩን የመጨረሻ ውሳኔ እነዲያገኝ ማድረግ ብቻ ነበር፡፡ በመሆኑም የእነተወልደና የእነሰዬ ቡድን ጠቅላላ ጉባዔ ይጠራ የሚል ፔቲሽን ተፈራርሞ አስገባ፡፡…የአቶ መለስ ቡድን አደጋውን በመፍራት ቀድመን እናባራቸው የሚል ሃሳብ ሲያቀርቡ ይህማ ህገ-ደንቡን መታስ ነው ይሆናል የሚል ተቃውሞ ሲመጣባቸው ‹‹የሕገ-ደንቡ አላማ ምንድን ነው የሚል የፍልስፍናዊ ጥያቄ አቀረቡ ‹‹የህገ ደንቡ ዓላማ  የድርጅቱን ሕልውና ማስጠበቅ ነው፤ አሁን በተፈጠረው ችግር ምክንያት ደግሞ ፓርቲው አደጋ ላይ ወድቋል ስለዚህ ሕገ ደንቡ የፓርቲውን ህልውና መጠበቅ በማይችለበት ጊዜ ከሕገ-ደንቡ ወጣ ብለን ፓርቲውን ማዳን አለብን አሉ››… ከዚያም አንጃ ተብለው የሚታወቁት ከፍተና አመራሮች ከፓርቲው ተባረሩ፡፡

·         ‹‹የ‹ሌጋሲ›ው ሥር ቁማርተኞች›› በአናንያ ሶሪ
·         ‹‹ደቂቀ- ‹‹ድምጻችን ይሰማ!›› በዮናስ በላይ
·         ‹‹እባካችሁ የህጻኑን አባት ልቀቁት›› በእንድርያስ ተረፈ

የኛ ፕሬስ ጋዜጣ (ረቡዕ ኅዳር 26 ቀን 2005 ዓ.ም)

·         ርዕሰ አንቀጽ፤ ‹‹ያልተፈተሹ መጻኢ አዲስ አበባ መከራዎች››
·         ዓባይ ዓባይ ማለት ያበዛው የኛ ፕሬስ ‹‹የናይል ግድብ ውዝግብ አልቀዘቀዘም›› ይለናል የግብጽ፣ የሱዳንና የኢትዮጵያ ኤክስፐርቶች በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ጉባዔ ያካሂዳሉ ቤንሻንጉል ተጉዘው ግድቡን ይጎበኛሉም ይለናል አሁንም ከሚታይባቸው ጉዳዮች አንዱ ግድቡ ስለሚከትለው ጉዳት ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግስት አሁንም ግድቡ ጉዳት አያስከትልም እያለ ነው፤ ይህ ነገር በሶስተኛ ወገን ጉዳት እንደሚደርስ ቢረጋገጥ ምን ይሆን የሚነገረን ፣ በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ዊኪሊክስን አላምን ብለው ከግብጽ ባለስልጣናት የተሰጣቸውን መረጃ ብቻ በመንተራስ ግብጽ በሱዳን ወታደራዊ ሰፈር የማቋቋም ዓላማ የላትም ብለዋል
·         ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ የመለስ ዜናዊን የስልጣን አወቃቀር አፈረሱ
·         ‹‹ለብቻቸው ጠቅልለውት የነበረውን ስልጣን አከፋፍለዋል›› የኛ ፕሬስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅም አላቸው ያንንም ተግባራዊ እያደረጉት ነው ብሎ እያዝናናን ነው፡፡
·         ‹‹ከሚንስትርነታቸው የተሰናበቱት አቶ ጁነዲን ሳዶ ከአ.አ.ዩ ቦርድ አባልነታቸው ተነሱ›› የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ካሳ ተክለብርሃን ተክተዋቸዋል፡፡
·         ‹‹የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሹመት አነጋጋሪ ሆኗል›› 
·         ‹‹ወደ ግብጽ ሊያመራ የነበረው የህዝብ ዲፕሎማሲ ጉዞ ተደናቀፈ›› ግብጾችም ልከዋልና እናም አይቅርብን በሚል በውጭ ጉዳይ የተቋቋመውና እነሰራዊት ፍቅሬን ያካተተው የሕዝብ ዲፕሎማሲ በግብጽ ሙርሲ ፈርኦን ነኝ ካላቸው ባኋላ በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት አለመረጋጋቱን ተከትሎ ጉዞው ሊደናቀፍ ችሏል፣ መቼስ ወጉ ባይቀርብንም መንግስት ከፍሎ ጥብቅና ሚስቆማቸው ብሎገሮችና የሎቢ ሥራ ስልጣኑን ለማራዘም እንደሚሰሩለት የሚታወቅ ነው እናም ሁሉም በዜግነቱ ለሀገሩ የበኩሉን እንዲያበረክት ሊበረታታና ዜጎች ከውጭ የሚሰሙት መረጃ ከመንግስታቸው እንዲያገኙት ቢደረግ ዘመኑ አንዱ የሚጠይቀው ዲፕሎማሲ ነውና ሁሉን እንዲያሳትፍ መንግስት ለመዋጮ የሚፈልገንን ዜጎቹን የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማን ‹‹አባይ እንዲመለስልን›› እርሱም በተጠያቂነት እንዲያከናውን  እንላለን፡፡
·         ‹‹ሰው ለሰው ድራማ ተተራመሰ››፣ ‹‹ናርዶስ ስትቀየር የተነገረኝ ነገር የለም፣ የፍቅር ጥያቄ አቅርቦልኝ አልተቀበልኩትም፣ በግል መኖሪያ ቤቴ ውስጥ ሱሶችን እንዲያቆም ነግሬው ነበር›› አርቲስት ብስራት ገመቹ፤ ‹‹ሴትነቷን የመወንጀያ መሳልያ አድልጋ እየተጠቀመችበት ነው›› እርቲስት መስፍን ጌታቸው
·         አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፈራረሰ
o    አለባቸው ንጉሴ ፕሬዚዳንት ሆኑ፣የዶ/ር በዛብህ አለመመረጥ አነጋጋሪ ሆነ
o    ወ/ሮ ብስራት ጠናጋሻው ከኃላፊነታቸው ተነሱ፣ ዱቤ ጅሎ ስልጣናቸውን ሊስረክቡ ነው
o    አቶ አማኑኤል ስፖርት ኮሚሽኑን ዘለፉ፣ ‹‹በታክስ እየተቀጣን ነው›› አትሌት ገ/እግዚአብሔር
·         ‹‹ሆላንድ ካር መክሰሩን አናውቅም፤ የከሰረ ድርጅት በወረፋ መኪና መሸጥ አይችልም›› አቶ ዮናስ ዘውዱ

ሰንደቅ ጋዜጣ (ረቡዕ ኅዳር 26 ቀን 2005 ዓ.ም)

·         ርዕሰ አንቀጽ፤ ‹‹የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ላይ ግልጽ ምርመራ››
·         የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትሮች ውዝግብ መሥሪያ ቤቱን እያመሰው ነው
‹‹ከሁሉም እኔ የሚያስጠላኝ ለቋሚ ኮሚቴ የሚቀርበው ሪፖርት ውሸት ነው
ሲቪል ሰርቪስ የሚቀርበው ሪፖርት ውሸት ነው፤
እኛም ጋ ማኔጅመንት ስንገመግም የሚቀርበው ሪፖርት ውሸት መሆናቸው ነው››   አቶ ዳውድ መሀመድ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዲኤታ
·         በላሊበላ በቱሪስቶች መግቢያ ዋጋ ጭማሪ ሳቢያ የተነሳው ውዝግብ እንደቀጠለ ነው፡፡
·         ‹‹ኢትዮጲካሊንክ›› የመዝናኛና የመረጃ ፕሮግራም በዛሚ ኤፍ ኤም በኪል ሊመጣ ነው፡፡
·         ‹‹የአባቶች እርቅ ከሰማይ ሲርቅ›› በአጥናፉ አለማየሁ
·         የአዲሱ ሹመት ገጽታዎች…
·         ‹‹ም/ሚኒስትሮቹ አቶ ኃይለማርያምን መደገፍ ሲገባቸው ስልጣኑን እንደጸበል ነው የተራጩት›› ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ

ሪፖርተር ጋዜጣ (እሁድ ኅዳር 30 ቀን 2005 ዓ.ም)

·         ርዕሰ አንቀጽ፤  ‹‹ለሥርዓትና ለተቋማት ግንባታ ቅድሚያ ትኩረትና ርብርብ ይደረግ!!››
·         የአዲስ አበባ አስተዳደር ለሚድሮክ ሰጥቶት የነበረውን 6,400 ካሬ ሜትር መሬት ነጠቀ
·         ክልሎች አዲስ በወጣው የመሬት ሊዝ አዋጅ ምክንያት ምንም መሥራት አልቻልንም አሉ
·         የሽብርተኝነት ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው 29 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀጠሮ ተሰጣቸውቤተሰቦቻቸው የፍርድ ቤት ውሎአቸውን እንዲከታተሉ ተጠየቀ

·         የሐረር ቢራ ሥራ አስኪያጅ ኃላፊነታቸውን ለቀቁ

·         ካቢኔው ለመሬት ጥያቄ ምላሽ ባለመስጠቱ ባለሀብቶች አማረሩ

·         ሌላም፣ ሌላም…

[ማስታወሻ፤] ለኛ ከአዲስ (በ80 ኪሎሜትሮች) ወጣ ላልን ሰዎች አዲስ ፎርቹንና ካፒታል በዕለቱ መድረስ እየቻሉ በማግስቱ እየላኩ አስቸግረውናልና አንድ በሉልን፣ በዛም ምክንያት ስለነሱ ምንም ማለት አልቻልንም፤
·         ዘግይተውም ቢሆን ከጨማመሩበት ድረ-ገጻቸውን ይጎብኙ
·         መልካም ቀን!

No comments:

Post a Comment