Wednesday, February 25, 2015

በሴት ተከሳሾች የመብት ጥሰት አቤቱታ ላይ "ፍርድ ቤቱ" ሌላ ቀጠሮ ሰጠ

በሴት ተከሳሾች የመብት ጥሰት አቤቱታ ላይ "ፍርድ ቤቱ" ሌላ ቀጠሮ ሰጠ
በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙትን ጦማሪት ማህሌት ፋንታሁን እና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬን አያያዝ አስመልክቶ ለዛሬ

Edom Kassaye and Mahilet Fantahun
ተቀጥሮ የነበረው "የፍርድ ቤት" ውሎ የመብት ጥሰቱን አስመልክቶ የማረሚያ ቤቱን ምላሽ በጽሁፍ ለመስማት ነበር ፡፡ ነገር ግን እስር ቤቱ አስተዳደሮች ስብሰባ ላይ በመሆናቸው የጽሁፍ ምላሹ ስላልተፈረመበት ማቅረብ አልቻልንም በማለት የማረሚያ ቤቱ ተወካይ ነኝ ብለው የቀረቡት ዋና ሳጅን ድሪባ ሰበታ ተናግረዋል፡፡
ዋና ሳጅን ድሪባ የእስር ቤቱ የህግ ባለሞያ እና የሴቶች ክፍል ሰራተኛ ነኝ ፍርድ ቤቱ ከፈቀደ በቃል ምላሽ ልስጥ ያሉ ሲሆን አግባብ ያለው የአስተዳደር ሰው አይደሉም በሚል "ፍርድ ቤቱ" ሳይቀበላቸው ቀርቷል፡፡
በዚህም መሰረት "ፍርድ ቤቱ" የቃሊቲ እስር ቤት አስተዳደር መልሱን በጽሁፍ ይዞ እንዲቀርብ ለየካቲት 25 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡( March 4) በተያያዘ ዜና ዓቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ አለኝ ያለውንና ከወንጀል ክሱ ጋር አያይዞ ካቀረበው የማስረጃ ዝርዝር መካከል የሲ.ዲ ማስረጃውን በተመለከተ የተከሳሽ ጠበቆች እስካሁን ስላልደረሳቸው አንዲደርሳቸው በጽሁፍ ጥያቄ አቅርበዋል ፡፡ የጠበቆቸን ጥያቄ ተከትሎ አቃቤ ህግ የሲዲ ማስረጃዎቸቹን ለጠበቆች አንዲያደርስ "ፍርድ ቤቱ" ትዝዛዝ ሰጥቷል፡፡
የዞን9 ማስታወሻ - የሴት እስረኞች መንገላታት በተደጋጋሚ ተገልጾ እና ትእዛዝ ተሰጥቶበት ከመንግሰት በባሰ ጨቋኝ የሆነው "የቃሊቲው መንግሰት" አፈና ያልተሻሻለ አንደሆነ ይታወቃል፡፡ የፓለቲካ እስረኞች አያያዝ የዞን9 ተከሳሾችን ብቻ ሳይሆን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ጋዜጠኛ ርእዬት አለሙን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ የሁሉም ጥያቄ መሆኑ መብት ጥሰቱ በተዘዋዋሪ መንግሰት የሚክደውን ፓለቲካ እስረኛ የለም የሚለውን ሃሳብ በተግባር የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ጠንካራ አርምጃ በመውሰድ በሌሎች ጉዳዬች ላይ ያጣውን እምነት አመኔታ እና ስልጣን ቢያንስ የታራሚዎቸን መብት በማስከበር እንዲያሳየው አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ በዚህ የተገለለ የጭቆና አያያዝ ውስጥ ሆነው አንኳን ፈገግታቸው ለአፍታም ያልተገደበው ሴት እስረኛ እህቶቻችን እንደሆነ ከጭቆናው በላይ መሆናቸውን ካስመሰከሩ ቆይተዋል፡፡
አሁንም ስለሚያገባን እንናገራለን !
ዞን9

No comments:

Post a Comment