Monday, August 24, 2015

ሲጠበቅ የነበረው የፍርድ ቤት ውሎ በድጋሚ ለጷግሜ 2 ተቀጠረ።

በዛሬው እለት በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የፍርድ ቤት ውሎ በድጋሚ ለጷግሜ 2 ተቀጠረ።
በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ለመከላከል ወይም ሳይከላከሉ በነፃ ለመሰናበት ውሳኔ ዛሬ ለ35ተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት አራቱ በእስር የሚገኙት ጦማርያን በድጋሚ በተለዋጭ ቀጠሮ ተሸኝተዋል።
በዛሬው ውሎ ችሎቱ ያልተሰየመ ሲሆን ተከሳሾች እና ጠበቆች በቢሮ ተጠርተው ዳኞች ተሟልተው ስላልተገኙ ችሎቱ ለመሰየም አለመቻሉን ዶክመንቶችን ማየትና ውሳኔውን ፅፎ ማጠናቀቅ አሁንም እንዳልቻሉ በመግለፅ ዳኛ ዘሪሁን ለጷግሜ 2 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠታቸውን አሳውቀዋል።
መደበኛ የወንጀል ችሎት ከነሃሴ 15 ጀምሮ የተዘጋ ሲሆን የዞን9 ጦማርያን ከመዘጋቱ በኃላ በሁለተኛ ልዩ ቀጠሮ እና በአጠቃላይ 36ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ተመልሰው ይቀርባሉ ።

No comments:

Post a Comment